የGoogle ካርታዎች/የGoogle Earth ተጨማሪ የአገልግሎት ውል
መጨረሻ የተቀየረው፦ ጁላይ፣ 2022
Google ካርታዎችን/Google Earthን ለመጠቀም፣ (1) የGoogle የአገልግሎት ውልን እና (2) እነዚህን የGoogle ካርታዎች/Google Earth ተጨማሪ የአገልግሎት ደንቦች (“የካርታዎች/Earth ተጨማሪ ደንቦች”) መቀበል አለብዎት። የካርታዎች/Earth ተጨማሪ ደንቦች በዋቢነት የGoogle ካርታዎች/Google Earth የህግ ማሳሰቢያዎችን እና Google ካርታዎች/Google Earth ኤፒአዮችን ያካትታል።
እባክዎን እያንዳንዱን ሰነድ በጥንቃቄ ያንብቡ። እነዚህ ሰነዶች በአንድ ላይ «ደንቦች» በመባል ይታወቃሉ። እርስዎ አገልግሎቶቻችንን ሲጠቀሙ ከእኛ የሚጠብቋቸውን ነገሮች፣ እና እኛ ከእርስዎ የምንጠብቃቸውን ነገሮች ይመሰርታሉ።
የንግድ መገለጫዎን ለማስተዳደር በGoogle ካርታዎች ውስጥ የነጋዴ-ብቻ ባህሪያትን የሚጠቀሙ ከሆነ https://support.google.com/business/answer/9292476 ላይ ያሉት Google የንግድ መገለጫ ደንቦች እርስዎን ይመለከታሉ።
ምንም እንኳ የእነዚህ ደንቦች አካል ባይሆንም እንዴት የእርስዎን መረጃ ማዘመን፣ ማስተዳደር፣ ወደ ውጭ መላክ እና መሰረዝ እንደሚችሉ በተሻለ ሁኔታ መረዳት እንዲችሉ የእኛን የግላዊነት መመሪያ እንዲያነብቡ እንመክራለን።
License. እነዚህን ውሎች እስከተከተሉ ድረስ፣ የGoogle የአገልግሎት ውሎች Google ካርታዎች/Google Earthን የመጠቀም ፈቃድ ይሰጡዎታል፣ ይህም የሚከተሉትን ለማድረግ የሚያስችሉዎትን ባህሪያት ያካትታል፦
ካርታዎችን ማየትና ማብራሪያ ማድረግ፤
KML ፋይሎችንና የካርታ ንብርብሮችን መፍጠር፤ እና
በመስመር ላይ፣ በቪድዮ እና በህትመት አማካኝነት ተገቢውን እውቅና በመስጠት ይዘትን በይፋ ማሳየት።
በGoogle ካርታዎች/Google Earth ማድረግ ስለተፈቀደልዎት የተለዩ ነገሮች ተጨማሪ ዝርዝሮችን ለማግኘት፣ እባክዎ የGoogle ካርታዎች፣ Google Earth እና የመንገድ እይታ አጠቃቀም የፈቃዶች ገጽን ይመልከቱ።
የሚከለከል ምግባር። ይህንን ክፍል 2 ማክበርዎ Google ካርታዎች/Google Earthን ለመጠቀም የፈቃድዎ ቅድመ ሁኔታ ነው። Google ካርታዎች/Google Earthን ሲጠቀሙ እርስዎ (ወይም እርስዎን የሚወክሉ) እነዚህን ማድረግ አይችሉም፦
የGoogle ካርታዎችን/Google Earthን የትኛውንም ክፍል እንደገና ማሰራጨት ወይም መሸጥ ወይም Google ካርታዎችን/Google Earthን መሰረት በማድረግ ምርት ወይም አገልግሎት መፍጠር (የእነርሱን የአገልግሎት ውል መሰረት በማድረግ የGoogle ካርታዎች/Google Earth ኤፒአይን የሚጠቀሙ ካልሆነ በስተቀር)፤
ይዘት መቅዳት (ይህን ለማድረግ በየGoogle ካርታዎች፣ የGoogle Earth እና የመንገድ እይታ አጠቃቀም የፈቃዶች ገጽ ወይም «ፍትሃዊ አጠቃቀምን» ጨምሮ በሚመለከታቸው የአዕምሮ ንብረት ህጎች ካልተፈቀደልዎ በስተቀር)፤
ይዘት በብዛት ማውረድ ወይም የጅምላ ምገባ (ወይም ሌላ ሰው ይህን እንዲያደርግ መፍቀድ)፤
የGoogle ካርታዎች/Google Earth አገልግሎቶችን ሊተኩ ወይም ትርጉም ባለው ደረጃ ተመሳሳይነት ያላቸው አገልግሎቶችን ሊሰጥ የሚችል ሌላ ማንኛውንም ከካርታ ጋር ግንኙነት ያለው የውሂብ ስብስብ ለመፍጠር ወይም ለማገዝ Google ካርታዎች/Google Earth መጠቀም (ይህም ሲባል የካርታ ወይም የአሰሳ ውሂብ ስብስብ፣ የንግድ ዝርዝሮች ውሂብ፣ የአድራሻ ዝርዝር፣ ወይም የቴሌማርኬቲንግ ዝርዝር ያካትታል)፤ ወይም
ከአሁናዊ አሰሳ ወይም እራሱን በራሱ ከሚቆጣጠር ተሽከርካሪ ጋር በተገናኝ ማናቸውንም የGoogle ካርታዎች/Google Earth ምርት ከሌሎች አካላት ምርቶች ጋር መጠቀም፣ ውስን የሆኑ በGoogle የቀረቡ እንደ Android Auto አይነት ባህሪያትን በመጠቀም ካልሆነ በስተቀር።
ነባራዊ ሁኔታዎች፤ ሃላፊነትን መውሰድ። ከGoogle ካርታዎች Google Earth ካርታ ውሂብ፣ ትራፊክ፣ አቅጣጫዎች እና ሌሎችንም ሲጠቀሙ፣ ነባራዊ ሁኔታዎች ከካርታው ውጤቶች ወይም ይዘት ሊለዩ ስለሚችሉ የእራስዎን ማገናዘብ መጠቀም ይኖርብዎታል እናም በGoogle ካርታዎች/Google Earth ሲጠቀሙ በእራስዎ ሃላፊነት ነው። በማንኛውም ጊዜ ለእራስዎ ምግባር እና ለሚኖሩት ውጤቶች ሃላፊነቱ የእርስዎ ነው።
Google ካርታዎች/Google Earth ውስጥ ያለ የእርስዎ ይዘት በGoogle ካርታዎች/Google Earth አማካኝነት የሚሰቅሉት፣ የሚያስገቡት፣ የሚያከማቹት፣ የሚልኩት ወይም የሚቀበሉት ይዘት በGoogle የአገልግሎት ውል የሚገዛ ይሆናል፣ ይህም «የእርስዎን ይዘት የመጠቀም ፈቃድ» የሚለው ክፍል ውስጥ ያለውን ፈቃድ ያካትታል። የፈረንሳይ ነዋሪ ከሆኑ፣ የGoogle ፍለጋ ተጨማሪ የአገልግሎት ውል በGoogle ፍለጋ ላይ በይፋ እንዲገኝ የተደረገ ተመሳሳይ ይዘት ላይ ተግባራዊ ይሆናል። ነገር ግን፣ በመሳሪያዎ ላይ ብቻ ተወስኖ የሚቀር ይዘት (እንደ በመሳሪያ ላይ የሚቀመጥ KML ፋይል) ወደ Google አይሰቀልም ወይም አይገባም፣ እናም ያ ፈቃድ አይመለከተውም።
የመንግስት ተጠቃሚዎች። Google ካርታዎችን/Google Earthን የመንግስት አካልን ወክለው የሚጠቀሙ ከሆነ፣ የሚከተሉት ውሎች ተፈጻሚ ይሆናሉ።
ገዢ ህግ።
በዩናይትድ ስቴትስ ወይም በአውሮፓ ህብረት ሀገራት ውስጥ ለሚገኙ የከተማ ወይም የግዛት መንግስት አካላት፣ በGoogle የአገልግሎት ውል ውስጥ ገዢ ህጎችን እና ቦታ በተመለከተ የቀረበው ክፍል ተግባራዊ አይሆንም።
ለዩናይትድ ስቴትስ የፌደራል መንግስት አካላት፣ በGoogle የአገልግሎት ውል ክፍል የቀረበው የገዢ ህግና ቦታ የተመለከ ይዘት ሙሉ በሙሉ በሚከተለው ተቀይሯል፦
«እነዚህ ውሎች የህግ አለመጣጣም መነሻ ሳይኖር፣ በዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ህጎች መሰረት ገዢ ይሆናል፣ ይተረጎማል እንዲሁም ተግባራዊ ይደረጋል። የፌደራል ህግ በሚፈቅደው ልክ ብቻ፦ (ሀ) አግባብነት ያለው የፌደራል ህግ በማይኖርበት ጊዜ የካሊፎርንያ ግዛት ህጎች (የካሊፎርንያን የህግ አለመጣጣም ህጎች ሳያካትት) ተግባራዊ ይደረጋሉ፤ እና (ለ) እነዚህን ውሎች ወይም Google ካርታዎች /Google Earthን በሚመለከት ለሚነሳ ማንኛውም ክርክር ካሊፎርንያ በሚገኘው የሳንታ ክላራ ካውንቲ የፌደራል ፍርድ ቤት በብቸኝነት የሚታይ ሲሆን ባለጉዳዮቹ በእነዚህ ፍርድ ቤቶች የግለሰባዊ ስልጣን ተስማምተዋል።»
የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት የተገደቡ መብቶች። በዩናይትድ ስቴትስ የፌደራል መንግስት የGoogle ካርታዎች/Google Earthን ማየት ወይም መጠቀም በየGoogle ካርታዎች/Google Earth የህግ ማሳሰቢያዎች ውስጥ ባለው «የዩናይትድ ስቴትስ የመንግስት የተገደቡ መብቶች» ክፍል ተገዢ ይሆናል።