የመንገድ እይታ የታመኑ ፎቶግራፍ አንሺዎች መመሪያ

ይህ መመሪያ Google ምርቶች ላይ ለመጠቀም ደንበኞቻቸውን ወክለው ምስል የሚሰበስቡ ሁሉንም የመንገድ እይታ የታመኑ ተሳታፊዎችን ይመለከታል።

የእኛ የመንገድ እይታ የታመኑ ፎቶግራፍ አንሺዎች መመሪያ አራት አካባቢዎችን ይሸፍናል፦


የግልጽነት መስፈርቶች

ደንበኞች Google ምርቶች ላይ ምስል የመስቀል ጥቅሞችን ሙሉ በሙሉ እንዲገነዘቡ፣ በመረጃ የተደገፈ ውሳኔ ለማድረግ ትክክለኛ መረጃ ማግኘት አለባቸው። ስለዚህ፣ ሁሉም የእኛ የታመኑ ተሳታፊዎች እነዚህ ውሳኔዎች ላይ ተጽዕኖ ያላቸው መረጃዎች ላይ ግልጽ እንዲሆኑ እንጠይቃለን። ከታች የተገለጹ መስፈርቶችን ከማሟላት በተጨማሪ፣ የታመኑ ተሳታፊዎች በሚጠየቅበት ጊዜ ሌሎች ተገቢ መረጃዎችን ለደንበኞቻቸው ለማቅረብ አግባብ ያላቸው ጥረቶችን ማድረግ ይኖርባቸዋል።

የፎቶግራፍ አገልግሎቶችዎን ለሌሎች ሲሸጡ፣ ተመሳሳይ ግልጽነትን እርስዎም መላበስዎ እና ግዴታዎችዎን እና መብቶችዎን ከሌሎች ሰዎች፣ የምርት ስሞች እና የአካባቢ ህጎች አንጻር ምን አንድምታ እንደሚኖራቸው መረዳትዎ በጣም አስፈላጊ ነው።


የGoogle ምርት ስሞችን በተገቢው ሁኔታ መጠቀም

የታማኝነት ደረጃን ያገኙ ፎቶ አንሺዎች ወይም ኩባንያዎች ብቻ የGoogle ካርታዎች የመንገድ እይታ የምርት ስምን እና የታማኝነት ባጅን እንደ የሽያጭ እሴቶች መጠቀም ይችላሉ። እንደ የታመነ ባለሙያ፣ ልዩ በሚያደርግዎ ሁኔታ ለመደሰት ለበለጠ ጥቅምዎ እንዲያውሏቸው እንጋብዝዎታለን። የታመኑ ባለሙያዎች የታማኝነት ባጅ፣ ልዩ የቃል ምልክት እና Google ካርታዎችን እና የመንገድ እይታን ወይም ሌሎች ተዛማጅ አርማዎችን ጨምሮ የምርት ስያሜ ክፍሎችን መጠቀም ይችላሉ። እነዚህን በመጠቀም ማከናዎን የሚችሏቸው እና የማይችሏቸው የተወሰኑ ነገሮች ከታች ቀርበዋል። የሆነ ሰው የGoogle የተፈቀደ የምርት ስም እሴቶቻችንን አጠቃቀም እየጣሰ እንደሆነ የሚያምኑ ከሆነ፣ ችግሮችን እዚህ ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ። ለሌሎች ሁሉም የGoogle የምርት ስም እሴቶች፣ አግባብነት የሌላቸው አጠቃቀሞችን እዚህ ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ።


የታመነ የምስል ጥራት መስፈርቶች


የተከለከሉ ድርጊቶች


ስለ እኛ መመሪያዎች

የGoogle የመንገድ እይታ የታመነ ፎቶግራፍ አንሺ መመሪያ ላይ ራስዎን ማለማመድ እና ወቅታዊ መረጃ ማግኘት አስፈላጊ ነው። የእኛን መመሪያዎች እየጣሱ መሆኑን ካመንን፣ የድርጊቶችዎን ዝርዝር ግምገማ ለማከናወን እርስዎን ልናነጋግር እና የእርምት እርምጃ ልንጠይቅ እንችላለን። ተደጋጋሚ ወይም ከባድ ጥሰቶች ሲኖሩ፣ ከታማኝነት ፕሮግራሙ እርስዎን ልናስወጣ እና በዚያው መሰረትም ለደንበኛዎችዎ ለማሳወቅ ልናነጋግራቸው እንችላለን። እንዲሁም ለGoogle ካርታዎች ምርቶች አስተዋጽዖ ከማበርከት ልንከለክልዎ እንችላለን።

እነዚህ መመሪያዎች ሶስተኛ ወገኖችን ሊመለከቱ ከሚችሉ ማንኛውም ነባር ውሎች እና መመሪያዎች በተጨማሪ ያሉ ናቸው፣ እነዚህን ጨምሮ፦