በዙሪያዎ ያለውን ዓለም እርስዎ እንዲያገኙ ለማገዝ Google ቁርጠኛ ነው። በመሳሪያ ስርዓቶቻችን ላይ የሚገኘው ምስል በአቅራቢያዎ ወይም በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ቦታዎችን አስቀድመው እንዲመለከቱ እና እንዲያስሱ በማገዝ የላቀ ልምድ እንዲያገኙ ለማድረግ የታሰበ ነው። ምስል ጠቃሚ መሆኑን እና ተጠቃሚዎቻችን የሚያስሱትን ዓለም የሚያንጸባርቅ መሆኑን ለማረጋገጥ ረጅም ርቀት ሄደናል።
የመንገድ እይታ ምስል በውጫዊ አካላት ወይም በGoogle ሊበረከቱ ይችላሉ። ከእያንዳንዱ ምሰል ጋር ከሚቀርበው የባለቤትነት ስም ወይም ከአዶው ልዩነቱን መናገር ይችላሉ። በውጫዊ አካል የተነሳ እና Google ካርታዎች ላይ የታተመ ምስል በዚያ አስተዋጽዖ አበርካች (ወይም እሱ በሰየመው በማንኛውም ምትክ) በባለቤትነት የተያዘ ነው።
ይህ ገጽ በGoogle የተበረከተ የመንገድ እይታ ምስል መመሪያን በግልጽ ያስቀምጣል። በተጠቃሚ ለተበረከተ የመንገድ እይታ ምስል፣ እባክዎ የካርታዎች በተጠቃሚ የተበረከተ ይዘት መመሪያን።
በGoogle የተበረከተ የመንገድ እይታ
የምስል መመሪያ
የመንገድ እይታ ምስልን የሚመለከት ሁሉም ሰው አዎንታዊ የሆነ ጠቃሚ ተሞክሮ እንዲኖረው ማረጋገጣችንን ለማገዝ ይህን በGoogle የተበረከተ የመንገድ እይታ መመሪያ አዘጋጅተናል። አግባብነት የሌለውን ይዘት እንዴት እንደምናስተናግድ እና የመንገድ እይታ ምስልን በGoogle ካርታዎች ላይ ለማተም የምንጠቀምባቸውን መስፈርቶች ይገልጻል። አልፎ አልፎ መመሪያችንን ስለምናዘምን፣ እባክዎ በየጊዜው እየተመለሱ ይመልከቱ።
የመንገድ እይታ ምስል የአሁናዊ አይደለም
የመንገድ እይታ ምስል የሚያሳየው ካሜራዎቻችን በአካባቢው ባለፉበት ቀን ላይ ማየት የቻሉትን ብቻ ነው። ከዚያም በኋላ፣ እነዚህን ምስሎች ለማቀነባበር ወራት ይፈጃል። ይህ ማለት የሚያዩት ይዘት ከጥቂት ወራት እስከ ጥቂት ዓመታት የሚደርስ ዕድሜ ያለው ሊሆን ይችላል። እንዲሁም ለበርካታ ዓመታት ምስል በሰበሰብንባቸው የተወሰኑ አካባቢዎች ላይ በእኛ የጊዜ ማሽን ተግባር ውስጥ በዚያ ምስል ላይ የተደረጉ ለውጦችን ማየት ይችላሉ
ማደብዘዝ
የመንገድ እይታ ምስል በGoogle ካርታዎች ላይ በሚታተምበት ጊዜ የግለሰቦችን ግላዊነት ለመጠበቅ Google በርካታ እርምጃዎችን ይወስዳል።
በመንገድ እይታ ውስጥ በGoogle-የተበረከቱ ምስሎች ውስጥ ያሉ የሚታወቁ መልኮችን እና የሰሌዳ ቁጥሮችን ለማደብዘዝ የተነደፈ የመጠቀ የፊት እና የሰሌዳ ቁጥር ማደብዘዣ ቴክኖሎጂ ገንብተናል። ፊትዎ ወይም የሰሌዳ ቁጥርዎ ተጨማሪ ማደብዘዝ የሚያስፈልገው መሆኑን ከተመለከቱ ወይም ሙሉ ቤትዎን፣ መኪናዎን ወይም ሰውነትዎን እንድናደበዝዝልዎ ከፈለጉ «ችግር ሪፖርት አድርግ» መሣሪያን በመጠቀም ጥያቄ ያቅርቡ።
አግባብነት የሌለው ይዘት
«ችግር ሪፖርት አድርግ» አገናኝን በመጠቀም አግባብነት የሌለው ይዘትን ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ። በይዘቱ ላይ ስነ-ጥበባዊ፣ ትምህርታዊ ወይም ጥናታዊ ዋጋ ከሌላቸው በስተቀር የሚከተሉትን ምድቦች አግባብነት የሌላቸው ይዘቶች አድርገን እንቆጥራቸዋለን።
የአእምሮ ንብረት ጥሰቶች
የቅጂ መብትን ጨምሮ በሌላ ማንኛውም ሰው ህጋዊ መብቶች ላይ ጥሰት የሚያስከትሉ ምስሎችን ወይም ሌላ ይዘትን አንፈቅድም። ለተጨማሪ መረጃ ወይም የዲኤምሲኤ ጥያቄ ፋይል ለማድረግ፣ የእኛን የቅጂ መብት አሰራሮች ይገምግሙ።
ወሲባዊ ልቅነትን የሚያሳይ ይዘት
ወሲባዊ ልቅነትን የሚያሳይ ይዘት አንፈቅድም።
ህገ ወጥ፣ አደገኛ ወይም ሁከት ያለው ይዘት
በተፈጥሮው ህገወጥ የሆነ፣ አደገኛ ወይም የወንጀል ድርጊቶችን የሚያበረታታ ወይም አስፈሪ የሆነ ወይም አስፈላጊ ያልሆኑ ሁከቶችን ያካተተ ይዘትን አንፈቅድም።
ትንኮሳ እና ማስፈራራቶች
የመንገድ እይታን ግለሰቦችን ለመተንኮስ፣ ለማጥቃት ወይም ጉዳት ለማድረስ የሚጠቀም ይዘትን አንፈቅድም።
የጥላቻ ንግግር
በዘር፣ በብሔር፣ በሃይማኖት፣ በአካል ጉዳት ሁኔታ፣ በጾታ፣ በእድሜ፣ በዜግነት፣ በውትድርና አገልግሎት ሁኔታ፣ በፆታዊ ዝንባሌ ወይም ፆታዊ ማንነት ላይ በመመርኮዝ በግለሰቦች ወይም በቡድኖች ላይ ብጥብጥን የሚያበረታታ ወይም የሚታገስ ይዘትን አንፈቅድም።
የአሸባሪ ይዘት
አሸባሪ ድርጅቶች ይህን አገልግሎት ምልመላን ጨምሮ ለማንኛውም ዓላማ እንዲጠቀሙበት አንፈቅድም። እንዲሁም ከሽብርተኝነት ጋር የተዛመደ ይዘትን፣ ለምሳሌ የሽብርተኝነት ድርጊቶችን የሚያበረታታ፣ ጥቃትን የሚያነሳሳ ወይም የሽብር ጥቃቶችን የሚያወድስ ይዘትን እናስወግዳለን።
ልጅን ለአደጋ ማጋለጥ
በህጻናት ላይ ብዝበዛ ወይም ጥቃት የሚያደርስን ይዘት በተመለከተ Google ፍጹም ያለመታገስ መመሪያ አለው። ይህም ወሲብ-ነክ ጥቃት የሚያደርሱ ሁሉንም ምስሎች እና ህጻናቱን ወሲብ-ነክ በሆነ መንገድ የሚያሳይ ሁሉንም ይዘት ይመለከታል። ህጻናትን በዚህ መልኩ ለብዝበዛ ያጋልጣል ብለው የሚያስቡት ይዘት ካጋጠመዎት፣ እባክዎ ይህን ይዘት እንደገና አያጋሩ እንዲሁም አስተያየት አያስቀምጡ፣ የእርስዎ ዓላማ ለGoogle ለማሳወቅ ቢሆንም እንኳን። በይነመረብ ላይ ሌላ ቦታ ይዘት ካገኙ፣ እባክዎ ብሔራዊ የጠፉ እና ብዝበዛ የደረሰባቸው ህጻናት ማዕከልን (ኤንሲኤምኢሲ) በቀጥታ ያነጋግሩ።
የግል ማንነትን ለይቶ ማወቅ የሚያስችል መረጃ
የራስዎንም ይሁን የሌላ ሰው እንደ የክሬዲት ካርድ ዝርዝሮች፣ የህክምና መረጃዎች ወይም በመንግስት የተሰጡ መታወቂያዎች ያለ የግል ማንነትን ለይቶ ለማወቅ የሚያስችል መረጃን ያካተተ ይዘት አንፈቅድም።