ይህ ይዘት በማህደር ከተቀመጠው የግላዊነት መመሪያችን ስሪት የመጣ ነው። የአሁኑ የግላዊነት መመሪያችንን ለማግኘት እዚህ ይመልከቱ።
«የግል መረጃን ጨምሮ ከአንድ አገልግሎት የመጣ የግል መረጃ ከሌሎች የGoogle አገልግሎቶች ከመጣ የግል መረጃ ጋር ያዋህዳል»
ምሳሌዎች
- ለምሳሌ፣ ወደ የእርስዎ Google መለያ ገብተው ከሆነና Google ላይ ሲፈልጉ ከይፋዊው ድር የተገኙ የፍለጋ ውጤቶችን ከገጾች፣ ፎቶዎች እና ከጓደኛዎችዎ የGoogle+ ልጥፎች ጋር ማየት ይችላሉ፣ እና እርስዎ የሚያውቋቸው ሰዎች ወይም እርስዎን በGoogle+ ላይ የሚከተሉ ሰዎች የእርስዎን ልጥፎች እና መገለጫ በውጤቶቻቸው ላይ ሊያዩ ይችላሉ። እንዲሁም እንደ Gmail ወይም Google ቀን መቁጠሪያ ባሉ የሚጠቀሙባቸው ሌሎች የGoogle ምርቶች ባሉ ይዘቶች ውስጥ ተገቢ መረጃ ማግኘትም ይችላሉ።
- ወደ ጣልያን ለመጓዝ ካሰቡ እና በGoogle ላይ «florence» ብለው ከፈለጉ ስለፍሎረንስ ያሉ የጓደኛዎችዎን ፎቶዎች ወይም ጽሑፎች በፍለጋ ውጤቶችዎ ውስጥ ማየት ይችላሉ። እነዚህ ውጤቶች የእነሱን ምክሮች ማሰስ እና የትኛዎቹ የመታያ ስፍራዎች መታየት እንዳለባቸው ላይ ውይይትን ለማስጀመር ቀላል ሊያደርጉ ይችላሉ። ተጨማሪ ይወቁ።
- Google Now በሌሎች የGoogle ምርቶች ላይ አከማችተው ሊሆኑ የቻሉትን ውሂብ ሊጠቀም ይችላል። ለምሳሌ፣ በእርስዎ የድር ታሪክ ላይ ፍለጋዎችን አከማችተው ከሆኑ Google Now በእነዚያ ያለፉ ፍለጋዎች ላይ ተመስርቶ በስፖርት ውጤቶች፣ የበረራ ሁኔታ እና የመሳሰሉት ላይ የተመሠረቱ የመረጃ ካርዶችን ሊያሳይ ይችላል። የድር ታሪክዎን ለማቀናበር google.com/history/ ይጎብኙ። የድር ታሪክዎን መሰረዝ ወይም ባለበት አቁመው Google Nowን መጠቀም ይችላሉ፣ ነገር ግን አንዳንድ የመረጃ አይነቶች አይታዩም። ተጨማሪ ይወቁ።
- ለአንድ የንግድ ቀጠሮ የGoogle ቀን መቁጠሪያ ግቤት ካለዎት Google Now የትራፊክ ሁኔታውን ተመልክቶ ቀጠሮዎን በሰዓቱ እንዲደርሱበት መቼ መነሳት እንዳለብዎት ሊጠቁምዎ ይችላል።