ይህ ይዘት በማህደር ከተቀመጠው የግላዊነት መመሪያችን ስሪት የመጣ ነው። የአሁኑ የግላዊነት መመሪያችንን ለማግኘት እዚህ ይመልከቱ።
«መረጃ መሰብሰብ»
ምሳሌዎች
- ይሄ እንደ የእርስዎ የአጠቃቀም ውሂብ እና ምርጫዎች፣ የGmail መልዕክቶች፣ የG+ መገለጫ፣ ፎቶዎች፣ ቪዲዮዎች፣ የአሰሳ ታሪክ፣ የካርታ ፍለጋዎች፣ ሰነዶች ወይም ሌሎች በGoogle የተስተናገዱ ይዘቶች ያሉ መረጃዎችን ያካትታል። የእኛ ራስ-ሰር ስርዓቶች ይህ መረጃ እንደተላከ፣ እንደደረሰ እና ሲከማች ይተነትኑታል።
- ይሄ ማንኛውም በስርዓቶቻችን በኩል የሚያልፍ ይዘትን ያካትታል። ለምሳሌ፣ የበረራ ማሳወቂያዎችን እና የተመዝግቦ መግቢያ አማራጮችን ለእርስዎ ለማቅረብ በእርስዎ የGmail ገቢ መልዕክት ሳጥን ውስጥ ያለ መረጃ፣ ከክበቦችዎ ጋር በኢሜይል ለመገናኘት በእርስዎ የGoogle+ መገለጫ ውስጥ ያለ መረጃ፣ እና ይበልጥ ተገቢ የሆኑ የፍለጋ ውጤቶችን ለእርስዎ ለማቅረብ በእርስዎ የድር ታሪክ ኩኪዎች ውስጥ ያለ መረጃ ልንጠቀም እንችላለን።