Android የተደራሽነት ጥቅል የAndroid መሣሪያዎን ከአይን ነፃ ወይም በመቀየሪያ መሣሪያ እንዲጠቀሙ የሚያግዝዎ የተደራሽነት መተግበሪያዎች ስብስብ ነው።
የAndroid የተደራሽነት ጥቅል እነዚህን ያካትታል፦
• የተደራሽነት ምናሌ፦ ስልክዎን ለመቆለፍ፣ ድምፅንና ብሩህነትን ለመቆጣጠር፣ ቅጽበታዊ ገጽ ዕይታዎችን ለማንሳት እና ሌሎችን ለማድረግ ይህን ትልቅ የማያ ገጽ ላይ ምናሌ ይጠቀሙ።
• ለመናገር ምረጥ፦ በማያ ገጽዎ ላይ ንጥሎችን ይምረጡ እና ጮክ ተደርገው ሲነበቡ ይስሟቸው።
• የTalkBack ማያ ገጽ አንባቢ፦ የቃል ግብረመልስ ያግኙ፣ መሣሪያዎን በምልክቶች ይቆጣጠሩ፣ እና በማያ ገጽ ላይ በብሬይል የቁልፍ ሰሌዳ ይተይቡ።
ለመጀመር፦
1. የመሣሪያዎን የቅንብሮች መተግበሪያን ይክፈቱ።
2. ተደራሽነትን ይምረጡ።
3. የተደራሽነት ምናሌን፣ ለመናገር ምረጥን ወይም TalkBack ይምረጡ።
Android የተደራሽነት ጥቅል Android 6 (Android M) ወይም ከዚያ በላይ ይጠይቃል። ለWear TalkBackን ለመጠቀም፣ Wear OS 3.0 ወይም ከዚያ በላይ ያስፈልግዎታል።
የፍቃድ ማሳወቂያ
• ስልክ፦ ማሳወቂያዎችን ለጥሪዎ ሁኔታ ማስተካከል እንዲችል Android የተደራሽነት ጥቅል የስልክ ሁኔታን ይከታተላል።
• የተደራሽነት አገልግሎት፦ ይህ መተግበሪያ የተደራሽነት አገልግሎት ስለሆነ፣ የእርስዎን እርምጃዎች መከታተል፣ የመስኮት ይዘትን መልሶ ማግኘት እና እርስዎ የሚጽፉትን ጽሁፍ መከታተል ይችላል።
• ማሳወቂያዎች፦ ይህን ፈቃድ ሲፈቅዱ TalkBack ስለ ዝማኔዎች ሊያሳውቅዎ ይችላል።