Google ዜና እርስዎ ተጨማሪ ቅድሚያ የሚሰጧቸውን ታሪኮች ማግኘት እንዲችሉ በዓለም ላይ እየተከሰቱ ያሉ ነገሮችን አደራጅቶ የሚያደምቅልዎ ግላዊነት የተላበሰ የዜና አዋሃድ ነው።
በGoogle News አማካኝነት እነዚህን ያገኛሉ፦
የእርስዎ የዜና አጭር ማጠቃለያ፦ ቅድሚያ የሚሰጡትን እያንዳንዱ ታሪክ መከታተል የማይቻል ሊሆን ይችላል፣ የእርስዎ የዜና አጭር ማጠቃለያ በዓለምዎ ውስጥ ያለው አስፈላጊ እና የሚመለከተዎት ነገር እያወቁ መቆየት ያቀልለዋል። ከፍተኛዎቹን አካባቢያዊ፣ ብሔራዊ እና የአለም አርዕስተ ዜናዎችንና እንዲሁም ለእርስዎ ፍላጎቶች የተበጁ ግላዊነት የተላበዙ ዜናዎችን ለእርስዎ ለማምጣት በዕለት ውሎዎ ላይ ያዘምነዎታል።
አካባቢያዊ ዜና፦ በእርስዎ አካባቢ ውስጥ ካሉ የዜና ምንጮች በመጡ ታሪኮች እና ዘገባዎች በኩል ማህበረሰብዎን ያስሱ። ከእርስዎ አጠገብ ወይም ቤትዎ የትም ይሁን ምን እየተከሰተ እንዳለ እንዲያውቁ ያብጁ እና በርካታ አካባቢዎችን ይምረጡ።
ሙሉ ሽፋን፦ በርካታ እተያየቶችን ይዘው ወደ አንድ ታሪክ ይበልጥ ጠልቀው ይግቡ። የሙሉ ሽፋን ባህሪው መስመር ላይ ስላለ አንድ ታሪክ ያለ ሁሉንም ነገር ያደራጃል፣ በዚህም ከተለያዩ ምንጮች እና ሚዲያዎች የመጣ ሽፋንን ያመጣል እና ያደምቃል። አንዴ መታ በማድረግ ብቻ ታሪኩ እንዴት እየተቀየረ እንዳለ እና ሁሉም ሰው እንዴት ሪፖርት እያደረገው እንዳለ ያውቃሉ።
ለእርስዎ የሆኑ ታሪኮች፦ የለእርስዎ ክፍሉ ከፍላጎቶችዎ ጋር የሚዛመድ ግላዊነት የተላበሰ ዜናን ያደርስልዎታል። እርስዎ ቅድሚያ የሚሰጧቸውን ርዕሰ ጉዳዮች እና ምንጮች በመከተል የሚመለከቷቸውን ዘገባዎች ይቆጣጠሩ እና ያብጁ።
ከማንኛውም መሳሪያ ሆነው ይድረሱ፦ Google ዜና የተለያዩ ስልኮች እና የግንኙነት ደረጃ ያላቸው የተጠቃሚዎች ፍላጎቶችን ለማሟላት የተነደፈ ነው። የእርስዎ ግንኙነት ጠንካራ ካልሆነ ወይም ውሂብ መቆጠብ ካስፈለገዎት Google ዜና የምስሎች መጠንን በመቀነስ እና ያነሰ ውሂብን በማውረድ በተለሳለሰ ሁኔታ መስራቱን ይቀጥላል። እርስዎ በኋላ ላይ ከመስመር ውጪ ሲሆኑ ዘገባዎች እንዲቀመጡ በWi-Fi በኩል ይወርዳሉ።
ዜናዎን በእርስዎ ላፕቶፕ ወይም ዴስክቶፕ ነው መድረስ የሚፈልጉት? የGoogle ዜና ሞባይል መተግበሪያውን ከዴስክቶፕ ድር ጣቢያችን news.google.com ጋር ያጣምሩት፣ በዚህም እንደተዘመኑ መቆየት እና በየትኛውም መሳሪያ ላይ ቢሆኑም ዜናውን መድረስ ይችላሉ።