ድምፅ ማጉያ የእርስዎን የAndroid ስልክ እና የራስ ላይ ማዳመጫዎች ብቻ በመጠቀም የመስማት ችግር ላላቸው ሰዎች የየዕለት ውይይቶችን እና የዙሪያ ድምፆችን የበለጠ ተደራሽ ያደርጋል። በመሣሪያዎ ላይ እንዲሁም በእርስዎ ዙሪያ ያሉ ድምጾችን ለማጣራት፣ ለማላቅ እና ለማጉላት ድምፅ ማጉያን ይጠቀሙ።
ባህሪያት• ንግግርን የበለጠ ለማወቅ የማይፈለግ ጫጫታን ይቀንሱ።
• ከውይይት ሁነታ ጋር ጫጫታ በተሞላባቸው አካባቢዎች ውስጥ የአንድ ተናጋሪ ድምፅ ላይ ያተኩሩ። (Pixel 3 እና ከዛ በላይ ለሆኑ የሚገኝ።)
• ውይይቶችን፣ ቲቪ ወይም ሌክቸሮችን ያዳምጡ። ራቅ ብለው ለሚገኙ የኦዲዮ ምንጮች የብሉቱዝ የራስ ላይ ማዳመጫዎች ይመከራሉ። (የብሉቱዝ የራስ ላይ ማዳመጫዎች የዘገየ የድምፅ መተላለፍ ሊኖራቸው ይችላል።)
• የእርስዎ መሣሪያ ላይ ለሚጫወት ሚዲያ ወይም በዙሪያዎ ለሚገኝ ውይይት የማዳመጥ ተሞክሮዎን ለራስዎ ያብጁ። ጫጫታን መቀነስ ወይም ዝቅተኛ ወይም ከፍተኛ ሞገድ ያላቸው ወይም ጸጥ ያሉ ድምፆችን መጨመር ይችላሉ። ለሁለቱም ጆሮዎች ወይም ለእያንዳንዱ ጆሮ ለያይተው ምርጫዎችዎችን ያቀናብሩ።
• የተደራሽነት አዝራር፣ ምልክት ወይም ፈጣን ቅንብሮችን በመጠቀም ድምፅ ማጉያን ያብሩ እና ያጥፉ። ስለተደራሽነት አዝራር፣ ምልክት እና ፈጣን ቅንብሮች የበለጠ ይወቁ፦
https://support.google.com/accessibility/android/answer/7650693መስፈርቶች• ለAndroid 8.1 እና ከዚያ በኋላ ለመጡ የሚገኝ።
• የእርስዎን የAndroid መሣሪያ ከየራስ ላይ ማዳመጫዎች ጋር ያጣምሩ።
• ውይይት ሁነታ በአሁኑ ወቅት ለPixel 3 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ይገኛል።
በድምፅ ማጉያ ላይ ያለዎትን ግብረመልስ በኢሜይል ወደ sound-amplifier-help@google.com ይላኩልን። ድምፅ ማጉያን መጠቀም ላይ እገዛን ለማግኘት
https://g.co/disabilitysupport ላይ ከእኛ ጋር ይገናኙ።
የፈቃዶች ማሳወቂያ•
ማይክሮፎን፦ የማይክሮፎን ተደራሽነት ድምፅ ማጉያ ድምጹን ለማጉላት እና ለማጣራት ማሰናዳት እንዲችል ይፈቅድለታል። ምንም ውሂብ አልተሰበሰበም ወይም አልተከማቸም።
•
የተደራሽነት አገልግሎት፦ ይህ መተግበሪያ የተደራሽነት አገልግሎት ስለሆነ የእርስዎን ተግባራት መከታተል፣ የመስኮት ይዘት ሰርስሮ ማውጣት እንዲሁም እርስዎ የሚተይቡትን ጽሁፍ መከታተል ይችላል።